ምሳሌ 23:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እውነትን ግዛ፥ አትሽጣትም፥ ጥበብንና ተግሣጽን፥ ማስተዋልንም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እውነትን ግዛት እንጂ አትሽጣት፤ ጥበብን፣ ተግሣጽንና ማስተዋልን ገንዘብህ አድርግ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እውነትን ገንዘብህ አድርግ፥ አትሽጣትም፥ ጥበብን ተግሣጽን ማስተዋልንም ግዛ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እውነትን፥ ጥበብን፥ ተግሣጽን፥ ማስተዋልን ገንዘብ አድርጋቸው እንጂ አትተዋቸው። |
ለአላዋቂ ሰው ገንዘብ ለምንድን ነው? አላዋቂ ሰው ጥበብን ገንዘብ ማድረግ አይችልምና፥ ቤቱን የሚያስረዝም ሰው ለራሱ ጥፋትን ይሻል፤ ለመማርም የሚጨንቀው ወደ ክፉ ይወድቃል።
እናንተ የተጠማችሁ ሁሉ፥ ወደ ውኃ ሂዱ፤ ገንዘብም የሌላችሁ ሂዱና ግዙ፤ ብሉ፤ ያለ ገንዘብም ያለ ዋጋም የወይን ጠጅና ወተት ጠጡ።
“ደግሞ መንግሥተ ሰማያት በእርሻ ውስጥ የተሰወረውን መዝገብ ትመስላለች፤ ሰውም አግኝቶ ሰወረው፤ ከደስታውም የተነሣ ሄዶ ያለውን ሁሉ ሸጠና ያን እርሻ ገዛ።
የክርስቶስ የመስቀሉ ተግዳሮት ከግብፅ ሀብት ሁሉ ይልቅ እጅግ የሚበልጥ ባለጠግነት እንደሚሆን ዐውቆአልና፥ ዋጋውንም ተመልክቶአልና።
ባለ ጠጋ እንድትሆን በእሳት የነጠረውን ወርቅ፥ ተጐናጽፈህም የራቁትነትህ ኃፍረት እንዳይገለጥ ነጭ ልብስን፥ እንድታይም ዐይኖችህን የምትኳለውን ኵል ከእኔ ትገዛ ዘንድ እመክርሃለሁ።