ምሳሌ 22:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እሾህና ወጥመድ በጠማማ ሰው መንገድ ናቸው፤ ነፍሱን የሚጠብቅ ግን ከእነርሱ ያመልጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በክፉዎች መንገድ ላይ እሾኽና ወጥመድ አለ፤ ነፍሱን የሚጠብቅ ግን ከእነዚህ ይርቃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እሾህና ወጥመድ በጠማማ ሰው መንገድ ላይ ይገኛሉ፥ ነፍሱን ግን የሚጠብቅ ከእነርሱ ይርቃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በክፉዎች መንገድ ላይ እሾኽና ወጥመድ አለ፤ ራሱን የሚጠብቅ ግን ከእነርሱ ይርቃል። |
የሕይወት መንገዶች ከክፉ ያርቃሉ፤ የጽድቅ ጎዳና የዘመን ብዛት ነው። ትምህርትን የሚቀበል በበጎ ይኖራል። ተግሣጽን የሚጠብቅም ብልሃተኛ ይሆናል። መንገዶቹን የሚጠብቅ ሰውነቱን ይጠብቃል፥ ሕይወትንም የሚወድድ አፉን ይጠብቃል።
አምላካችሁ እግዚአብሔር ከሰጣችሁ ከዚህች ከመልካሚቱ ምድር እስክትጠፉ ድረስ መውደቂያና ወጥመድ፥ በእግራችሁም ችንካር፥ በዐይናችሁም እሾህ ይሆኑባችኋል እንጂ አምላካችሁ እግዚአብሔር ከእንግዲህ ወዲያ እነዚህን አሕዛብ ከፊታችሁ እንዳያጠፋቸው ራሳችሁ ዕወቁ።
ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኃጢአትን እንዳያደርግ፥ ነገር ግን ከእግዚአብሔር የተወለደው ራሱን እንዲጠብቅ ክፉውም እንዳይነካው እናውቃለን።