አባቶችህ የሠሩትን የቀድሞውን ድንበር አታፍርስ።
የቀድሞ አባቶችህ ያስቀመጡትን፣ የጥንቱን የወሰን ምልክት አታፋልስ።
አባቶችህ የሠሩትን የቀድሞውን የድንበር ምልክት አታፋልስ።
የቀድሞ አባቶችህ ያኖሩትን የወሰን ምልክት አትለውጥ።
ኃጥኣን የድንበሩን ምልክት አለፉ፤ እረኛውንም ከመንጋዎቹ ጋር ይነጥቃሉ።
አባቶችህ ያኖሩትን የድንበር ምልክት አታፍልስ፤ ወደ ድሃ አደጎች እርሻም አትግባ፤
ኃጥኣንን ወደ ጻድቃን ቦታ አትውሰድ፤ በሆድህ ጥጋብም አትሳሳት፥
“አምላክህ እግዚአብሔር ትወርሳት ዘንድ በሚሰጥህ ምድር፤ በምትካፈላት ርስትህ አባቶችህ የተከሉትን የባልንጀራህን የድንበር ምልክት አትንቀል።
“የባልንጀራውን የድንበር ምልክት የሚገፋ ርጉም ይሁን፤ ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይላሉ።