ተስፋህ በእግዚአብሔር ይሆን ዘንድ፥ መንገዱን ያሳውቅሃል።
ስለዚህ መታመኛህ በእግዚአብሔር ላይ እንዲሆን፣ ዛሬ አንተን ራስህን አስተምርሃለሁ።
እምነትህ በእግዚአብሔር ይሆን ዘንድ እነሆ እነርሱን ዛሬ አስታወቅሁህ።
እነርሱንም የማስተላልፍልህ እምነትህ በእግዚአብሔር እንዲሆን ብዬ ነው።
ነፍሴ በኋላህ ተከታተለች፥ እኔንም ቀኝህ ተቀበለችኝ።
ለዕውቀትና ለምክር ይሆኑህ ዘንድ ሦስት ነገሮችን እነሆ ጻፍሁልህ። አንተም በልብህ ሰሌዳነት ጻፋቸው።
በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታምነህ ኑር፥ በራስህም ጥበብ አትደገፍ፤
እነሆ፥ አምላኬ መድኀኒቴ ነው፤ ጌታ እግዚአብሔር ክብሬና ዝማሬዬ ነው፤ መድኀኒቴም ሆኖአልና በእርሱ ታምኜአለሁ፤ አልፈራምም።”
ጌታ እግዚአብሔር የዘለዓለም አንባ ነውና ለዘለዓለም በእግዚአብሔር ታመኑ።
በእግዚአብሔር የሚታመን፥ ተስፋውም እግዚአብሔር የሆነ ሰው ቡሩክ ነው።