የንጉሡም አገልጋዮች ገብተው፦ ‘እግዚአብሔር የሰሎሞንን ስም ከስምህ ይልቅ መልካም ያድርግ፤ ዙፋኑንም ከዙፋንህ የበለጠ ያድርግ’ ብለው ጌታቸውን ንጉሡ ዳዊትን መረቁ፤” ንጉሡም በአልጋው ላይ ሆኖ ሰገደ።
ምሳሌ 22:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መልካም ስም ከብዙ ባለ ጠግነት ይሻላል፥ መልካም ሞገስም ከብርና ከወርቅ ይበልጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መልካም ስም ከብዙ ብልጽግና ይመረጣል፤ መከበርም ከብርና ከወርቅ ይበልጣል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መልካም ስም ከብዙ ሃብት ይሻላል፥ መልካም ሞገስም ከብርና ከወርቅ ይበልጣል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መልካም ስም ከብዙ ሃብት ይሻላል፤ በሰው ዘንድ መወደድም ከብር ወይም ከወርቅ ይበልጣል። |
የንጉሡም አገልጋዮች ገብተው፦ ‘እግዚአብሔር የሰሎሞንን ስም ከስምህ ይልቅ መልካም ያድርግ፤ ዙፋኑንም ከዙፋንህ የበለጠ ያድርግ’ ብለው ጌታቸውን ንጉሡ ዳዊትን መረቁ፤” ንጉሡም በአልጋው ላይ ሆኖ ሰገደ።
ከመከራውም ሁሉ አዳነው፤ በግብፅ ንጉሥ በፈርዖን ፊትም ሞገስንና ጥበብን ሰጠው፤ በግብፅና በቤቱ ሁሉ ላይ ቢትወደድ አድርጎ ሾመው።
ወንድሜና አጋዤ ስትሪካ ሆይ፥ እንድትረዳቸው አንተንም እለምንሃለሁ፤ ወንጌልን በማስተማር ከቀሌምንጦስና ሥራቸው ከተባበረ፥ ስማቸውም በሕይወት መጽሐፍ ከተጻፈላቸው ከወንድሞቻችንም ሁሉ ጋር ከእኔም ጋር ደክመዋልና።