La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ምሳሌ 21:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግዚአብሔር ለጠማሞች ጠማማ ሥራን ይልክባቸዋል፤ ሥራው የቀናና ንጹሕ ነውና።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የበደለኛ መንገድ ጠማማ ነው፤ የንጹሕ ሰው ጠባይ ግን ቀና ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የበደለኛ መንገድ የጠመመች ናት፥ የንጹሕ ሥራ ግን የቀና ነው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ኃጢአተኞች በጠማማ መንገድ መሄድ ይወዳሉ፤ ልበ ንጹሖች ግን መልካም የሆነውን ነገር ያደርጋሉ።

Ver Capítulo



ምሳሌ 21:8
25 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ምድ​ርን እንደ ተበ​ላ​ሸች፥ ሥጋን የለ​በሱ ሁሉም በም​ድር ላይ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውን እንደ አበ​ላሹ አየ።


ዐመፃን ማሰብ በእግዚአብሔር ዘንድ የተናቀ ነው፤ የንጹሓን ቃል ግን ያማረ ነው።


መንገዳቸው ጐጻጕጽ፥ አካሄዳቸው ጠማማ ለሆኑ ወዮላቸው!


ከነዝናዛ ሴት ጋር በተለሰነ ቤት ከመቀመጥ ይልቅ፥ ከቤት ውጭ በማዕዘን ላይ መቀመጥ ይሻላል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጊ​ዜው ሰዎ​ችን ቅኖች አድ​ርጎ እንደ ሠራ​ቸው እነሆ፥ ይህን ብቻ አገ​ኘሁ፥ እነ​ርሱ ግን ብዙ ዕው​ቀ​ትን ይሻሉ።


ከፀ​ሓይ በታች የተ​ደ​ረ​ገው ክፉ ሁሉ ለሁሉ ነው፤ የሁሉ ድርሻ አንድ ነውና። ደግ​ሞም የሰው ልጆች ልብ ክፋ​ትን ትሞ​ላ​ለች፥ በሕ​ይ​ወ​ታ​ቸው ሳሉ ሁከት በል​ባ​ቸው አለ፥ ከዚ​ያም በኋላ ወደ ሙታን ይወ​ር​ዳሉ።


የጻ​ድ​ቃን መን​ገድ የቀና ትሆ​ና​ለች፤ የቅ​ኖ​ችም መን​ገድ ትጠ​ረ​ጋ​ለች።


የሰ​ላ​ምን መን​ገድ አያ​ው​ቁም፤ በመ​ን​ገ​ዳ​ቸ​ውም ፍርድ የለም፤ የሚ​ሄ​ዱ​በ​ትም መን​ገድ ጠማማ ነው፤ ሰላ​ም​ንም አያ​ው​ቁም።


“ዛፍ ከፍሬዋ ትታወቃለችና ዛፍዋን መልካም፥ ፍሬዋንም መልካም አድርጉ፤ ወይም ዛፍዋን ክፉ ፍሬዋንም ክፉ አድርጉ።


ልበ ንጹሖች ብፁዓን ናቸው፤እግዚአብሔርን ያዩታልና።


ልባ​ቸ​ው​ንም በእ​ም​ነት አን​ጽቶ ከእኛ አል​ለ​ያ​ቸ​ውም።


በሥ​ጋዊ ሕግም ትኖ​ራ​ላ​ች​ሁና እርስ በር​ሳ​ችሁ የም​ት​ቃ​ኑና የም​ት​ከ​ራ​ከሩ ከሆነ ግን ሥጋ​ው​ያን መሆ​ና​ችሁ አይ​ደ​ለ​ምን? እንደ ሰው ልማ​ድስ የም​ት​ኖሩ መሆ​ና​ችሁ አይ​ደ​ለ​ምን?


ሁሉ ለንጹሖች ንጹሕ ነው፤ ለርኵሳንና ለማያምኑ ግን ንጹሕ የሆነ ምንም የለም፤ ነገር ግን አእምሮአቸውም ሕሊናቸውም ረክሶአል።


መድኃኒታችንም ከዐመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።


እኛ ደግሞ አስቀድመን የማናስተውል ነበርንና፤ የማንታዘዝ፥ የምንስት፥ ለምኞትና ለልዩ ልዩ ተድላ እንደ ባሪያዎች የምንገዛ፥ በክፋትና በምቀኝነት የምንኖር፥ የምንጣላ፥ እርስ በርሳችን የምንጠላላ ነበርን።


እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ፥ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለ ነበረው ሥራ አይደለም፤


ጻድቅ እንደ ሆነ ካወቃችሁ ጽድቅን የሚያደርግ ሁሉ ከእርሱ እንደ ተወለደ እወቁ።


በእርሱም ይህን ተስፋ የሚያደርግ ሁሉ እርሱ ንጹሕ እንደ ሆነ ራሱን ያነጻል።