ከቍጡ፥ ከነዝናዛና ከነገረኛ ሴት ጋር ከመቀመጥ ይልቅ በምድረ በዳ መቀመጥ ይሻላል።
ከጨቅጫቃና ከቍጡ ሚስት ጋራ ከመኖር፣ በምድረ በዳ መኖር ይሻላል።
ከጠበኛና ከቁጡ ሴት ጋር ከመቀመጥ በምድረ በዳ መቀመጥ ይሻላል።
ከጨቅጫቃና ከነዝናዛ ሚስት ጋር አብሮ ከመኖር በምድረ በዳ መኖር ይሻላል።
አላዋቂ ልጅ ለአባቱ ኀፍረት ነው፥ ከዐስበ ደነስ ጋር የሚቀርብ ስእለትም ንጹሕ አይደለም።
ከነዝናዛ ሴት ጋር በተለሰነ ቤት ከመቀመጥ ይልቅ፥ ከቤት ውጭ በማዕዘን ላይ መቀመጥ ይሻላል።
ሁሉም አመንዝሮች፥ የዐመጸኞች ጉባኤ ናቸውና ሕዝቤን እተዋቸው ዘንድ ከእነርሱም እለይ ዘንድ በምድረ በዳ ማደሪያን ማን በሰጠኝ?