ምሳሌ 21:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍርድን ማድረግ ለጻድቃን ደስታ ነው፤ ጻድቅ ሰው ግን ክፉ በሚሠሩ ዘንድ የረከሰ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፍትሕ ሲሰፍን ጻድቁን ደስ ያሠኘዋል፤ ክፉ አድራጊዎችን ግን ያሸብራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፍርድን ማድረግ ለጻድቅ ደስታ ነው፥ ኃጢአትን ለሚያደርጉ ግን ጥፋት ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ትክክለኛ ፍርድ በሚሰጥበት ጊዜ ደጋግ ሰዎች ደስ ይላቸዋል፤ ክፉዎችን ግን ያስደነግጣል። |
በቸርነትህ የሚታገሡ መንገድህንም የሚያስቡ ይገናኙሃል፤ እነሆ፥ አንተ ተቈጣህ፤ እኛም ኀጢአት ሠራን፤ ስለዚህም ተሳሳትን።
ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፥ “የእኔስ መብል የላከኝን የአባቴን ፈቃድ አደርግ ዘንድ፥ ሥራውንም እፈጽም ዘንድ ነው።