የእግዚአብሔርም ብርሃን በጥዋት፥ በማለዳም ፀሐይ ይወጣል፤ ብርሃኑም በነግህ ይመጣል፤ ከዝናምም የተነሣ በምድር ሐመልማል ይለመልማል።
ምሳሌ 20:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እውነተኛ ንጉሥ በዙፋኑ በተቀመጠ ጊዜ በዐይኖቹ ፊት ምንም ክፉ አይቃወመውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሥ ለፍርድ ዙፋኑ ላይ በሚቀመጥበት ጊዜ፣ ክፉውን ሁሉ በዐይኖቹ አበጥሮ ይለያል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በፍርድ ወንበር የተቀመጠ ንጉሥ ክፉውን ሁሉ በዐይኖቹ ይበትናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በፍርድ ዙፋን ላይ የተቀመጠ ንጉሥ ክፉ የሆነውን ነገር ሁሉ አበጥሮ የሚያውቅ ዐይን አለው። |
የእግዚአብሔርም ብርሃን በጥዋት፥ በማለዳም ፀሐይ ይወጣል፤ ብርሃኑም በነግህ ይመጣል፤ ከዝናምም የተነሣ በምድር ሐመልማል ይለመልማል።