ምሳሌ 20:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቸርነትና እውነት ንጉሥን ይጠብቁታል፤ ዙፋኑንም በእውነት ይከቡታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፍቅርና ታማኝነት ንጉሥን ይጠብቁታል፤ በፍቅርም ዙፋኑ ይጸናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቸርነትና እውነት ንጉሥን ይጠብቁታል፥ ዙፋኑም በቸርነት ይበረታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቸርነትና ታማኝነት ንጉሥን ይጠብቁታል፤ መንግሥቱም በእውነተኛነት ላይ ጸንቶ ይኖራል። |
እግዚአብሔር ያበራልኛል፥ ያድነኛልም፤ ምን ያስፈራኛል? እግዚአብሔር የሕይወቴ መታመኛዋ ነው፤ ምን ያስደነግጠኛል?
መድኃኒቴ በእግዚአብሔር ነው፤ ክብሬም በእግዚአብሔር ነው፥ የረድኤቴ አምላክ፥ ተስፋዬም እግዚአብሔር ነው።
ዙፋን በምሕረት ይጸናል፥ በዚያም ላይ በዳዊት ቤት ፍርድን የሚሻ ጽድቅንም የሚያፋጥን ፈራጅ በእውነት ይቀመጣል፤ ይፈርዳልም።