ሁለት ዓይነት ሚዛን በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነው፥ ሐሰተኛ ሚዛንም መልካም አይደለም።
ሁለት ዐይነት ሚዛን በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነው፤ አባይ ሚዛን አይወደድም።
ሁለት ዓይነት ሚዛን በጌታ ዘንድ አስጸያፊ ነው፥ ሐሰተኛ ሚዛንም መልካም አይደለም።
እግዚአብሔር ያልተስተካከለ መስፈሪያና ሐሰተኛ ሚዛን ይጸየፋል።
አባይ ሚዛን በእግዚአብሔር ፊት አስጸያፊ ነው፤ እውነተኛ ሚዛን ግን በእርሱ ዘንድ የተመረጠ ነው።
ሁለት ዐይነት ሚዛንና ሁለት ዐይነት መስፈሪያ፥ ሁለቱ በእግዚአብሔር ፊት ርኩሳን ናቸው። የሚሠራቸውም በሥራው ይሰነካከላል።
እውነተኛ ሚዛን፥ እውነተኛም የኢፍ መስፈሪያ፥ እውነተኛም የባዶስ መስፈሪያ ይሁንላችሁ።
ስለዚህ ወደ አምላክህ ተመለስ፤ ምሕረትንና ፍርድን ጠብቅ፤ ዘወትርም ወደ አምላክህ ቅረብ።
“እህልን እንሸጥ ዘንድ መባቻው መቼ ያልፋል? የኢፍ መስፈሪያውንም እያሳነስን፥ ሰቅሉንም እያበዛን፥ በሐሰተኛም ሚዛን እያታለልን፥
“በከረጢትህ ውስጥ ታላቅና ታናሽ ሚዛን አይኑርልህ።