ምሳሌ 20:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚሰማ ጆሮና የሚያይ ዓይን፥ ሁለቱ የእግዚአብሔር ሥራ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚሰሙ ጆሮዎች፣ የሚያዩ ዐይኖች፣ ሁለቱንም እግዚአብሔር ሠርቷቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚሰማ ጆሮንና የሚያይ ዓይንን፥ ሁለቱን ጌታ ፈጠራቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚሰማ ጆሮንና የሚያይ ዐይንን የፈጠረ እግዚአብሔር ነው። |
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “ለሰው አፍን የሰጠ ማን ነው? ዲዳስ፥ ደንቆሮስ፥ የሚያይስ፥ ዕውርስ የሚያደርግ ማን ነው? እኔ እግዚአብሔር አይደለሁምን?
ይኸውም ዐይናቸውን ትከፍትላቸው ዘንድ፥ ከጨለማም ወደ ብርሃን፥ ሰይጣንን ከማምለክም ወደ እግዚአብሔር ትመልሳቸው ዘንድ፥ ኀጢአታቸውም ይሰረይላቸው ዘንድ፥ በስሜም በማመን ከቅዱሳን ጋር አንድነትን ያገኙ ዘንድ ነው።’