ከእነርሱም ጋር ሲነጋገር እነሆ፥ መልእክተኛው ወደ እርሱ ደረሰ፤ እርሱም፥ “እነሆ፥ ይህ ክፉ ነገር ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው፥ እግዚአብሔርን ገና እጠብቅ ዘንድ ምንድን ነኝ?” አለ።
ምሳሌ 19:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰው ስንፍናው መንገዱን ያጣምምበታል፥ በልቡም እግዚአብሔርን ገፋኢ ያደርገዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰው በራሱ ቂልነት ሕይወቱን ያበላሻል፤ በልቡ ግን እግዚአብሔርን ያማርራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰው ስንፍና መንገዱን ታጣምምበታለች፥ ልቡም በጌታ ላይ ይቈጣል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ሰው በሞኝነቱ ጥፋት ሲደርስበት በእግዚአብሔር ላይ ያማርራል። |
ከእነርሱም ጋር ሲነጋገር እነሆ፥ መልእክተኛው ወደ እርሱ ደረሰ፤ እርሱም፥ “እነሆ፥ ይህ ክፉ ነገር ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው፥ እግዚአብሔርን ገና እጠብቅ ዘንድ ምንድን ነኝ?” አለ።
ሰነፍ ግን ስንፍናን ይናገራል፤ ልቡም ዐመፅን ያደርግ ዘንድ፥ በእግዚአብሔር ላይ ስሕተትን ይናገር ዘንድ፥ የተራበችውንም ሰውነት ይበትን ዘንድ፥ የተጠማችንም ነፍስ ባዶ ያደርግ ዘንድ ከንቱን ያስባል።
“እናንተ ግን፦ የጌታ መንገድ የቀናች አይደለችም ትላላችሁ። የእስራኤል ቤት ሆይ! እንግዲህ ስሙ፤ በውኑ መንገዴ የቀናች አይደለችምን? ይልቅስ የእናንተ መንገድ ያልቀናች አይደለችምን?
ሳሙኤልም ሳኦልን፥ “በድለኻል፤ አምላክህ እግዚአብሔር ያዘዘህን ትእዛዙን አልጠበቅህምና፤ ዛሬ እግዚአብሔር መንግሥትህን በእስራኤል ላይ ለዘለዓለም አጽንቶልህ ነበር።
ኀጢኣት እንደ ምዋርተኝነት ናትና አምልኮተ ጣዖትም ደዌንና ኀዘንን ያመጣል። የእግዚአብሔርን ቃል ንቀሃልና እግዚአብሔር ንጉሥ እንዳትሆን ናቀህ” አለው።