ምሳሌ 19:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፌዘኛን ብትገርፈው አላዋቂው ብልሃተኛ ይሆናል፤ አስተዋይን ሰው ብትገሥጸው ግን ዕውቀትን ያገኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፌዘኛን ግረፈው፤ አላዋቂውም ማስተዋልን ይማራል፤ አስተዋይን ዝለፈው፤ ዕውቀትን ይገበያል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፌዘኛ ብትገርፈው አላዋቂ ብልሃተኛ ይሆናል፥ አስተዋይን ሰው ብትገሥጸው እውቀትን ያገኛል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፌዘኛ ብትቀጣው አላዋቂው ብልኅ ይሆናል፤ አስተዋይ ሰው ብትገሥጸው የበለጠ ዕውቀትን ይጨምራል። |
አላዋቂ ልጅ የአባቱን ተግሥጽ ያቃልላል፤ ተግሣጽን የሚጠብቅ ግን ዐዋቂ ነው። እውነት ከበዛ ዘንድ ብዙ ኀይል አለ፥ ኀጢአተኞች ግን ከምድር ገጽ ይጠፋሉ፥
የከተማዉም ሰዎች ሁሉ በድንጋይ ደብድበው ይግደሉት፤ እንዲህም ክፉውን ነገር ከመካከልህ ታርቃለህ፤ እስራኤልም ሁሉ ሰምተው ይፈራሉ።