ታካች ሰው እጁን በብብቱ ይሸሽጋል፥ ወደ አፉ ስንኳ አይመልሳትም።
ሰነፍ እጁን ወጭት ውስጥ ያጠልቃል፤ ወደ አፉ ግን መመለስ እንኳ ይሳነዋል።
ታካች ሰው እጁን በወጭቱ ያጠልቃታል፥ ወደ አፉ ስንኳ አይመልሳትም።
አንዳንድ ሰዎች በጣም ሰነፎች ናቸው፤ ሌላው ቀርቶ በወጥ ያጠቀሱትን እንጀራ መጒረስ ይታክታቸዋል።
ታካች ሰው አድኖ አይዝም። ንጹሕ ሰው ግን ክቡር ሀብት ነው።
የሰነፎች መንገዶች እሾህ የተከሰከሰባቸው ናቸው፥ የጽኑዓን መንገዶች ግን ጥርጊያ ናቸው።
ችግረኛን ሰው ሽብር ይይዘዋል፥ የማይሠራ ሰውም ይራባል።
ታካችን ምኞቱ ትገድለዋለች፥ እጆቹ ምንም ይሠሩ ዘንድ አይፈቅዱምና።
እርሱም መልሶ “ከእኔ ጋር እጁን በወጭቱ ያጠለቀ፥ እኔን አሳልፎ የሚሰጥ እርሱ ነው።
እርሱም መልሶ “ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ ከእኔ ጋር ወደ ወጭቱ እጁን የሚያጠልቀው ነው።