እኔም ዛሬ ዘመዱ እንደ ሆንሁ፥ እርሱም በንጉሡ ዘንድ የተሾመ እንደ ሆነ አታውቁምን? እነዚህም ሰዎች የሦርህያ ልጆች በርትተውብኛል፤ እግዚአብሔርም ክፋት በሠራ ላይ እንደ ክፋቱ ይመልስበት” አላቸው።
ምሳሌ 19:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለአላዋቂ ቅምጥልነት አይገባውም፥ አገልጋይም ከስድብ ጋር ቢገዛ ይበረታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሞኝ ተንደላቅቆ መኖር አይገባውም፤ ባሪያ የመሳፍንት ገዥ ከሆነማ የቱን ያህል ይከፋ! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለሰነፍ ቅምጥልነት አይገባውም፥ ይልቁንም ባርያ በአለቆች ላይ ይገዛ ዘንድ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሞኞች በድሎት መኖር አይችሉም፤ የባሪያ በመኳንንት ላይ ገዢ መሆንማ ምንኛ የከፋ ነው? |
እኔም ዛሬ ዘመዱ እንደ ሆንሁ፥ እርሱም በንጉሡ ዘንድ የተሾመ እንደ ሆነ አታውቁምን? እነዚህም ሰዎች የሦርህያ ልጆች በርትተውብኛል፤ እግዚአብሔርም ክፋት በሠራ ላይ እንደ ክፋቱ ይመልስበት” አላቸው።
ሕዝብ በሕዝብ ላይ፥ ሰው በሰው ላይ፥ ሰውም በባልንጀራው ላይ ይገፋፋል፤ ብላቴናውም በሽማግሌው ላይ፥ የተጠቃውም በከበርቴው ላይ ይታበያል።
እስራኤል ሆይ! ከአምላክህ ርቀህ አመንዝረሃልና እንደ አሕዛብ ደስ አይበልህ፤ ሐሴትንም አታድርግ፤ ከእህሉና ከወይኑ አውድማ ሁሉ ይልቅ የግልሙትና ዋጋን ወድደሃል።
አቤግያም ወደ ናባል መጣች፤ እነሆም፥ በቤቱ እንደ ንጉሥ ግብዣ ያለ ግብዣ ያደርግ ነበር፤ ናባልም እጅግ ሰክሮ ነበርና ልቡ ደስ ብሎት ነበር፤ ስለዚህም እስኪነጋ ድረስ ታናሽ ነገር ወይም ታላቅ ነገር አልነገረችውም ነበር።