በሥራው ራሱን የማያድን፥ ራሱን ለሚያጠፋ ወንድም ነው።
ለሥራው ደንታ የሌለው ሰው፣ የአጥፊ ወንድም ነው።
በሥራው ታካች የሚሆን የሀብት አጥፊ ወንድም ነው።
ሰነፍ ሰው ከአጥፊ ሰው ተለይቶ አይታይም፤
ለሌሊት ዎፍ ወንድም፥ ለሰጎንም ባልንጀራ ሆንሁ።
የሐኬተኛ እጅ ችግረኛ ያደርጋል፤ የትጉህ እጅ ግን ባለጠጋ ያደርጋል።
ፍርሀት ሰነፎችን ይጥላል፥ የተቸገሩ ሰዎች ሰውነትም ይራባል።
ችግረኛን ሰው ሽብር ይይዘዋል፥ የማይሠራ ሰውም ይራባል።
ጌታውም መልሶ እንዲህ አለው ‘አንተ ክፉና ሃኬተኛ ባሪያ፥ ካልዘራሁባት እንዳጭድ ካልበተንሁባትም እንድሰበስብ ታውቃለህን?
ለሥራ ከመትጋት አትስነፉ፤ በመንፈስ ሕያዋን ሁኑ፤ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤
ዳተኞች እንዳትሆኑ በሃይማኖትና በትዕግሥት ተስፋቸውን የወረሱትን ሰዎች ምሰሉአቸው።