እነዚህም ደግሞ በንጉሡ በዳዊትና በሳዶቅ በአቤሜሌክም በሌዋውያንና በካህናት አባቶች ቤቶች አለቆች ፊት፥ ታላላቆች እንደ ታናናሽ ወንድሞቻቸው፥ እንደ ወንድሞቻቸው እንደ አሮን ልጆች ዕጣ ተጣጣሉ።
ምሳሌ 18:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዕጣ ክርክርን ያስተዋል፥ በኀያላንም መካከል ይለያል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዕጣ መጣጣል ሙግትን ያስቆማል፤ ኀይለኛ ባላንጣዎችንም ይገላግላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዕጣ ክርክርን ትከለክላለች፥ በኃያላንም መካከል ትበይናለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዕጣ መጣል ጠብን ያበርዳል፤ ሁለት ጠንካራ ተከራካሪዎችንም ይገላግላል። |
እነዚህም ደግሞ በንጉሡ በዳዊትና በሳዶቅ በአቤሜሌክም በሌዋውያንና በካህናት አባቶች ቤቶች አለቆች ፊት፥ ታላላቆች እንደ ታናናሽ ወንድሞቻቸው፥ እንደ ወንድሞቻቸው እንደ አሮን ልጆች ዕጣ ተጣጣሉ።
የሕዝቡም አለቆች በኢየሩሳሌም ተቀመጡ፤ ከቀሩትም ሕዝብ ከዐሥሩ ክፍል አንዱ በቅድስቲቱ ከተማ በኢየሩሳሌም፥ ዘጠኙም በሌሎች ከተሞች ይቀመጡ ዘንድ ዕጣ ተጣጣሉ።
ሳኦልም እግዚአብሔርን፥ “የእስራኤል አምላክ ሆይ፥ ለእኔ ለባሪያህ ዛሬ ያልመለስህልኝ ስለ ምንድን ነው? ይህች በደል በእኔ፥ በልጄ በዮናታንም እንደ ሆነች አቤቱ የእስራኤል አምላክ ሆይ፥ ተናገር። ዕጣው ይህን የሚገልጥ ከሆነ ለሕዝብህ ለእስራኤል እውነትን ግለጥ፥” አለ። ዕጣም በዮናታንና በሳኦል ላይ ወጣ፤ ሕዝቡም ነፃ ወጣ።
ሳኦልም፥ “በእኔና በዮናታን መካከል ዕጣ አጣጥሉን፤ እግዚአብሔር ዕጣ ያወጣበትም ይሞታል” አላቸው። ሕዝቡም ሳኦልን፥ “እንዲህ ያለ ነገር አይሆንም” አሉት፤ ሳኦልም ሕዝቡን እንቢ አላቸው። በእርሱና በልጁ በዮናታን መካከልም ዕጣ አጣጣሉ። ዕጣውም በልጁ በዮናታን ላይ ወጣ።