ሻካራ ቃልን ከመናገር የሚከለክል ዐዋቂ ነው፥ ትዕግሥተኛ ሰውም ብልህ ነው።
ዐዋቂ ሰው ንግግሩ ቍጥብ ነው፤ አስተዋይም መንፈሱ የረጋ ነው።
ጥቂት ቃልን የሚናገር አዋቂ ነው፥ መንፈሱም ቀዝቃዛ የሆነ አስተዋይ ነው።
ንግግሩን የሚቈጥብ ዐዋቂ ነው፤ የረጋ መንፈስ ያለውም ሰው አስተዋይ ነው።
ኃጥእ ከነገር ብዛት የተነሣ ከኀጢአት አያመልጥም፤ ከንፈሩን የሚገታ ግን አስተዋይ ነው።
ትዕግሥተኛ ሰው ጥበብ የበዛለት ይሆናል፤ ትዕግሥት የጐደለው ሰው ግን ሰነፍ ነው፤
የጻድቃን ልብ ታማኝነትን ይማራል፤ የኃአጥኣን አፍ ግን ክፋትን ይመልሳል። የደጋግ ሰዎች መንገዶች በእግዚአብሔር ዘንድ የተወደዱ ናቸው፥ ስለ እነርሱም ጠላቶች ወዳጆችን ይሆናሉ።
ትዕግሥተኛ ሰው ከኀያል፥ ጥበብ ያለው ሰውም ሰፊ ርስት ካለው፥ በመንፈሱ የሠለጠነ ሰውም ሀገርን ከሚገዛ ሰው ይሻላል።
በስንፍና ከሚፈርዱ ፈራጆች ጩኸት ይልቅ የጠቢባን ቃል በጸጥታ ትሰማለች።
ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን፤
የጽድቅም ፍሬ ሰላምን ለሚያደርጉት ሰዎች በሰላም ይዘራል።
ሁላችን በብዙ ነገር እንሰናከላለንና፤ በቃል የማይሰናከል ማንም ቢኖር እርሱ ሥጋውን ሁሉ ደግሞ ሊገታ የሚችል ፍጹም ሰው ነው።