ኃጥኣን ግን በክፉ ቀን ይጠፋሉ።
የምታደርገውን ሁሉ ለእግዚአብሔር ዐደራ ስጥ፤ ዕቅድህም ሁሉ ይሳካልሃል።
ሥራህን ለጌታ አደራ ስጥ፥ አሳብህም ትጸናለች።
የጽድቅህንም ብድራት ይሰጥሃል። ብርሃንም በመንገድህ ላይ ይበራል።
“እኔ ግን እግዚአብሔርን እለምነው ነበር፥ የሁሉ ጌታ እግዚአብሔርንም እጠራው ነበር።
በመንገድህ ሁሉ ጥበብን ዕወቃት፥ እርስዋም መንገድህን ታቃናልሃለች።
ለደቀ መዛሙርቱም እንዲህ አላቸው፥ “ስለዚህ እላችህዋለሁ፤ ለነፍሳችሁ ስለምትበሉትና ስለምትጠጡት፥ ለሰውነታችሁም ስለምትለብሱት አትጨነቁ።
በምንም አትጨነቁ፤ ነገር ግን በሁሉ ነገር ጸልዩ ማልዱም፤ እያመሰገናችሁም ልመናችሁን ለእግዚአብሔር ግለጡ።
እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።