ይህንም ነገር አደርግና እበድል ዘንድ፥ በእኔም ላይ ክፋት እንዲናገሩና እንዲያላግጡ ያስፈራራኝ ዘንድ ተገዝቶ ነበር።
ምሳሌ 16:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ክፉ ሰው ወዳጆቹን ይዋሻል፥ መልካምም ወዳልሆኑ መንገዶች ይመራቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፉ ሰው ባልንጀራውን ያባብለዋል፤ መልካም ወዳልሆነውም መንገድ ይመራዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ግፈኛ ሰው ወዳጁን ያባብላል፥ መልካምም ወዳይደለ መንገድ ይመራዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዐመፀኛ ሰውን ያታልላል፤ ወደ ጥፋትም ይመራል። |
ይህንም ነገር አደርግና እበድል ዘንድ፥ በእኔም ላይ ክፋት እንዲናገሩና እንዲያላግጡ ያስፈራራኝ ዘንድ ተገዝቶ ነበር።
ራሱን የሚያውቅ ሰው ለራሱ ጻድቅ ነው፤ የክፉዎች ሥራ ግን መልካም አይደለም። የሚበድሉ ሰዎችን ክፉ ይከተላቸዋል፥ የኃጥኣን መንገዳቸውም ታስታቸዋለች።
ሳኦልም ዳዊትን ጠበቀው፤ በነጋው እንዲገድሉት መልእክተኞቹን ወደ ዳዊት ቤት ላከ፤ ሚስቱም ሜልኮል፥ “በዚህች ሌሊት ነፍስህን ካላዳንህ ነገ ትገደላለህ” ብላ ነገረችው።
ሳኦልም ሜልኮልን አላት፥ “ስለምን እንዲህ አታለልሽኝ? ጠላቴን አስኰበለልሽ፤ እንዲያመልጥም አደረግሽው?” ሜልኮልም ለሳኦል፥ “እርሱ፦ አውጥተሽ ስደጂኝ፤ አለዚያ እገድልሻለሁ አለኝ” አለችው።