እውነተኛ ምስክር ነፍስን ከክፉ ያድናል፥ ሐሰተኛ ግን ሐሰትን ያቀጣጥላል።
እውነተኛ ምስክር ሕይወት ያድናል፤ ሐሰተኛ ምስክር ግን አባይ ነው።
እውነተኛ ምስክር ነፍሶችን ያድናል፥ በሐሰት የሚናገር ግን ሸንጋይ ነው።
እውነትን የሚናገር ምስክር ሕይወትን ያድናል፤ ሐሰት የሚናገር ምስክር ግን አታላይ ነው።
ከጻድቅ ፍሬ የሕይወት ዛፍ ይወጣል። የዐመፀኞች ነፍሳት ግን በድንገት ይወገዳሉ።
ጻድቅ ሰው የተገለጠ እውነትን ያስተምራል፤ የክፉዎች ምስክርነት ግን ውሸት ነው።
የታመነ ምስክር አይዋሽም፤ የሐሰት ምስክር ግን ሐሰትን ያቀጣጥላል።
ሐሰተኛ ምስክር ሳይቀጣ አይቀርም፥ በግፍዕ የሚከስም አያመልጥም።
ወደ እግዚአብሔር መመለስንና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ማመንን ለአይሁድና ለአረማውያን እየመሰከርሁ፤
በመጨረሻው ዘመን እንደ ራሳቸው ምኞት የሚመላለሱ ዘባቾች በመዘበት እንዲመጡ ይህን በፊት እወቁ፤