ምሳሌ 14:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዐዋቂ ሰው የጠቢባን ዘውድ ነው፤ የአላዋቂዎች ተግባር ግን ክፉ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠቢባን ብልጽግና ዘውዳቸው ነው፤ የሞኞች ቂልነት ግን ፍሬው ከንቱነት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጠቢባን ዘውድ ባለጠግነታቸው ነው፥ የሰነፎች ስንፍና ግን ስንፍና ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የብልኆች ዘውድ ጥበባቸው ነው፤ የሞኞች ጌጥ ግን ሞኝነታቸው ነው። |
በድኅነታችን መዝገብ በሕግ ይሰበስቡአቸዋል፤ ጥበብና ምክር፥ ጽድቅም ከእግዚአብሔር ዘንድ ናቸው፤ እነዚህም የጽድቅ መዝገቦች ናቸው።
እኔም እላችኋለሁ፦ ባለቀባችሁ ጊዜ እነርሱ በዘለዓለም ቤታቸው ይቀበሉአችሁ ዘንድ በዐመፃ ገንዘብ ለእናንተ ወዳጆች አድርጉበት።