ኀጢአተኛ በተገለበጠበት ይጠፋል፥ የጻድቃን ቤቶች ግን ጸንተው ይኖራሉ።
ክፉ ሰዎች ይገለበጣሉ፤ ድራሻቸውም ይጠፋል፤ የጻድቃን ቤት ግን ጸንቶ ይኖራል።
ክፉ ሰዎች ይወድቃሉ፥ ፈጽሞም አይገኙም፥ የጻድቃን ቤት ግን ጸንቶ ይኖራል።
ዐመፀኞች ወድቀው ደብዛቸው ይጠፋል የደጋግ ሰዎች ትውልድ ግን ጸንቶ ይኖራል።
ቤቱ የታመነ ይሆናል፤ መንግሥቱም በፊቴ ለዘለዓለም፥ ዙፋኑም ለዘለዓለም ይጸናል።”
ስምህ ለዘለዓለም ታላቅ ይሁን።
የኃጥኣን መድኀኒታቸው ታልቃለች። ተስፋቸውንም ያጣሉ፥ የዝንጉዎች ዐይኖችም ይጠፋሉ።”
ሥራቸውን ያውቃል፥ በእነርሱም ላይ ሌሊትን ያመጣል፥ መከራንም ያጸናባቸዋል።
ልቤ ደነገጠብኝ፥ ኀይሌም ተወኝ፥ የዐይኖቼም ብርሃን ፈዘዘብኝ።
ኃጥእ እንደ ዐውሎ ነፋስ ኅልፈት ይጠፋል፤ ጻድቅ ግን ተሰውሮ ለዘለዓለም ይድናል።
በሐሰት እጅን በእጅ የሚመታ አይድንም፤ ጽድቅን የሚዘራ ግን የታመነ ዋጋን ያገኛል።
የብልህ ሰው አንደበት በሰው ሁሉ ዘንድ ይመሰገናል፤ ልበ ጠማማ የሆነ ሰው ግን ይናቃል።
ብልሆች ሴቶች ቤቶችን ይሠራሉ፤ ሰነፎች ሴቶች ግን በእጃቸው ያፈርሳሉ።
የክፉዎች ቤቶች ይፈርሳሉ፤ የቅኖች ማደሪያዎች ግን ይጸናሉ።
እግዚአብሔር የትዕቢተኞችን ቤት ያፈርሳል፤ የመበለቷን ወሰን ግን ያጸናል።