ታካች ሰው አድኖ አይዝም። ንጹሕ ሰው ግን ክቡር ሀብት ነው።
ሰነፍ ዐድኖ ያመጣውን እንኳ አይጠብስም፤ ትጉህ ሰው ግን ለንብረቱ ዋጋ ይሰጣል።
ታካች ሰው አደን ምንም አያድንም፥ ለሰው የከበረ ሀብት ትጋት ነው።
ሰነፍ ከሆንክ የምትመኘውን ማግኘት አትችልም፤ በትጋት ከሠራህ ግን ትበለጽጋለህ።
የጠላቶቼ መዘባበቻ አታድርገኝ ብያለሁና፥ እግሬም ቢሰናከል በእኔ ላይ ብዙ ነገርን ይናገራሉ።
የሐኬተኛ እጅ ችግረኛ ያደርጋል፤ የትጉህ እጅ ግን ባለጠጋ ያደርጋል።
ራሱን የሚያውቅ ሰው ለራሱ ጻድቅ ነው፤ የክፉዎች ሥራ ግን መልካም አይደለም። የሚበድሉ ሰዎችን ክፉ ይከተላቸዋል፥ የኃጥኣን መንገዳቸውም ታስታቸዋለች።
የማይሠራ ሁሉ በምኞት ይኖራል። የደጋጎች እጅ ግን ይተጋል።
እግዚአብሔርን በመፍራት የሚገኝ ጥቂት ሀብት እግዚአብሔርን ባለመፍራት ከሚገኝ ብዙ መዝገብ ይሻላል።
የእግዚአብሔር ሥራ ሁሉ ከእውነት ጋር ነው።
በእጅህ ተቀበል፥ እንደዚህም ታዘጋጅ ዘንድ እንዳለህ ዕወቅ።