ምሳሌ 12:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጻድቅ ሰው የተገለጠ እውነትን ያስተምራል፤ የክፉዎች ምስክርነት ግን ውሸት ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሐቀኛ ምስክር በእውነት ይመሰክራል፤ ሐሰተኛ ምስክር ግን ውሸት ይናገራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እውነተኛን ነገር የሚናገር ቅን ነገርን ያወራል፥ የሐሰት ምስክር ግን ተንኰልን ያወራል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እውነትን የሚናገር ሁሉ የታመነ ምስክርነትን ይሰጣል፤ ሐሰተኛ ምስክር ግን ሰውን ያታልላል። |
የምትሠሩት ነገር ይህ ነው፣ እያንዳንዳችሁ ከባልንጀራችሁ ጋር እውነትን ተነጋገሩ፣ በበር አደባባያችሁም የእውነትንና የሰላምን ፍርድ ፍረዱ፣
የሐሰት ምስክሮችንም አቆሙበት፤ እነርሱም እንዲህ አሉ፥ “ይህ ሰው በዚህ ቤተ መቅደስ ላይና በኦሪት ላይ የስድብ ቃል እየተናገረ ዝም በል ቢሉት እንቢ አለ፤