ጻድቅ ከወጥመድ ያመልጣል፥ ኀጢአተኛ ግን በእርሱ ፋንታ ይሰጣል።
ጻድቅ ከመከራ ይድናል፤ ይልቁን መከራው በክፉው ላይ ይደርሳል።
ጻድቅ ከጭንቀት ይድናል፥ ክፉ ግን የእርሱን ቦታ ይወስዳል።
ጻድቅ ከመከራ ይድናል። መከራው ግን በክፉ ሰው ላይ ይደርሳል።
ጻድቅ ሰው በሞተ ጊዜ ተስፋውን አያጣም፥ የክፉዎች ትምክሕታቸው ግን ትጠፋለች።
በክፉዎች አፍ የሀገር ወጥመድ አለ፥ የጻድቃን ዕውቀት ግን መልካም ጎዳና ናት።
ኀጢአተኛ ሰው በከንፈሩ ኀጢአት ወደ ወጥመድ ይወድቃል፤ ጻድቅ ግን ከእርሱ ያመልጣል። አስፍቶ የሚመለከት ሰው ብዙ ምሕረትን ያገኛል። ድንገት በበር የሚገናኝ ግን ነፍሳትን ያስጨንቃል።
ኃጥእ በጻድቅ ዘንድ የተናቀ ነው፥ ኃጥእም የጻድቅ ቤዛ ነው።