ምሳሌ 10:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔር በረከት በጻድቃን ራስ ላይ ነው። የኃጥኣንን አፍ ግን ኀዘን በድንገት ይዘጋዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በረከት በጻድቃን ራስ ላይ ነው፤ መዓት ግን የክፉዎችን አፍ ይዘጋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በረከት በጻድቅ ራስ ላይ ነው፥ የክፉዎች አፍ ግን ግፍ ይከድነዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደግ ሰው በረከትን ያገኛል፤ ክፉ ሰው ግን ዐመፀኛነቱን በመልካም አነጋገር ይሸፍናል። |
የተማረ ልጅ ብልህ ይሆናል። ሰነፍ ልጅ ግን ራሱን ተገዥ ያደርጋል። ብልህ ልጅ ከቃጠሎ ይድናል፤ ኀጢአተኛ ልጅ ግን በአውድማ ነፋስ የሚጨብጥ ይሆናል። ብልህ ልጅ በመከር ጊዜ ይሠራል። ሰነፍ ልጅ ግን በመከር ጊዜ ይተኛል።
ክፉ ምክርን መክረዋልና ለነፍሳቸው ወዮላት! እንዲህም አሉ፥ “ጻድቁን እንሻረው፤ ሸክም ሆኖብናልና፤” ስለዚህ የእጃቸውን ሥራ ፍሬ ይበላሉ።
አንደበት ሁሉ ይዘጋ ዘንድ፥ ዓለምም ሁሉ ከእግዚአብሔር ፍርድ በታች ይሆን ዘንድ ኦሪት የሚናገረው ሁሉ በኦሪት ላሉት እንደ ተነገረ እናውቃለን።