Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ምሳሌ 10:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 የተማረ ልጅ ብልህ ይሆናል። ሰነፍ ልጅ ግን ራሱን ተገዥ ያደርጋል። ብልህ ልጅ ከቃጠሎ ይድናል፤ ኀጢአተኛ ልጅ ግን በአውድማ ነፋስ የሚጨብጥ ይሆናል። ብልህ ልጅ በመከር ጊዜ ይሠራል። ሰነፍ ልጅ ግን በመከር ጊዜ ይተኛል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ሰብሉን በበጋ የሚሰበስብ ጠቢብ ልጅ ነው፤ በመከር ጊዜ የሚተኛ ግን ውርደት ይከተለዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 በበጋ የሚያከማች ልጅ አስተዋይ ነው፥ በመከር የሚተኛ ግን እርሱ ራሱን ያስነውራል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ብልኅ ሰው መከሩን በወቅቱ ይሰበስባል፤ በመከር ወራት የሚተኛ ግን ውርደት ይደርስበታል።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 10:5
10 Referencias Cruzadas  

መብሉን በበጋ ይሰበስባል፥ በመከርም ጊዜ በሰፊ ቦታ ያስቀምጣል። ወይም ወደ ንብ ሂድ፥ ሠራተኛ እንደ ሆነች፥ መልካም ሥራንም እንደምትሠራ ዕወቅ፥ የደከመችበትንም ነገሥታትና ሌሎች ሰዎች ለጤንነት ይወስዱታል። በሁሉም ዘንድ የተወደደች ናት፥ የከበረችም ናት። በአካሏ ደካማ ናት፥ በሥራዋ ግን የጸናች ናት፥ ጥበብን አክብራ አሳየች።


አባቱን የሚያዋርድ እናቱንም የሚያሳድድ፥ አሳፋሪና ጐስቋላ ልጅ ይሆናል።


ብልህ አገልጋይ አላዋቂዎች ጌቶችን ይገዛል፥ ከወንድማማች ጋርም ርስትን ይካፈላል።


ልባም ሴት ለባልዋ ዘውድ ናት፤ ክፉ ሴት ግን ነቀዝ እንጨትን እንደሚበላ እንዲዚሁ ባሏን ትጐዳለች።


አንተ ታካች፥ ወደ ገብረ ጕንዳን ሂድ፥ መንገዱንም ተመልክተህ ቅና። ከእርሱም ይልቅ ብልህ ሁን።


የሐኬተኛ እጅ ችግረኛ ያደርጋል፤ የትጉህ እጅ ግን ባለጠጋ ያደርጋል።


የእግዚአብሔር በረከት በጻድቃን ራስ ላይ ነው። የኃጥኣንን አፍ ግን ኀዘን በድንገት ይዘጋዋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios