“ብዙ እንደምትናገር እንዲሁ መስማት አለብህ። ወይስ በንግግርህ ብዛት ጻድቅ የምትሆን ይመስልሃልን? ከሴቶች የሚወለድ ዘመኑ ጥቂት የሆነ ቡሩክ ነው።
ምሳሌ 10:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኃጥእ ከነገር ብዛት የተነሣ ከኀጢአት አያመልጥም፤ ከንፈሩን የሚገታ ግን አስተዋይ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከቃላት ብዛት ኀጢአት አይታጣም፤ አንደበቱን የሚገታ ግን ጠቢብ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በቃል ብዛት ውስጥ መተላለፍ ሳይኖር አይቀርም፥ ከንፈሩን የሚገታ ግን አስተዋይ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከብዙ ንግግር ውስጥ ስሕተት አይጠፋም፤ ስለዚህ አስተዋይ ሰው ብዙ ከመናገር ይቈጠባል። |
“ብዙ እንደምትናገር እንዲሁ መስማት አለብህ። ወይስ በንግግርህ ብዛት ጻድቅ የምትሆን ይመስልሃልን? ከሴቶች የሚወለድ ዘመኑ ጥቂት የሆነ ቡሩክ ነው።
ወደ እግዚአብሔር ቤት በምትሄድበት ጊዜ እግርህን ጠብቅ፤ የጠቢባንንም ትምህርት ለመስማት ቅረብ፤ ዳግመኛም ከሰነፎች ስጦታ መሥዋዕት አድርገህ ከመቀበል ተጠበቅ፤ እነርሱ መልካም ለመሥራት ዐዋቂዎች አይደሉምና።
እግዚአብሔር በሰማይ፥ አንተም በምድር ነህና በአፍህ አትፍጠን፥ በእግዚአብሔርም ፊት ቃልን ይናገር ዘንድ ልብህ አይቸኩል፤ ስለዚህም ቃልህ ጥቂት ይሁን።