እርሱም ይህን ሲናገር ንጉሡ አሜስያስ፥ “በውኑ የንጉሡ አማካሪ ልትሆን ሹሜሃለሁን? ቅጣት እንዳያገኝህ ተጠንቀቅ” አለው። ነቢዩም፥ “ይህን አድርገሃልና፥ ምክሬንም አልሰማህምና እግዚአብሔር ሊያጠፋህ እንዳሰበ አወቅሁ” ብሎ ዝም አለ።
ምሳሌ 10:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተግሣጽ የሕይወትን መንገድ ይጠብቃታል፤ በተግሣጽ የማይዘለፍ ግን ይስታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ተግሣጽን ነቅቶ የሚጠብቅ የሕይወትን መንገድ ያሳያል፤ ዕርምትን የማይቀበል ግን ሌሎችን ወደ ስሕተት ይመራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተግሣጽን የሚጠብቅ በሕይወት መንገድ ይሄዳል፥ ዘለፋን የሚተው ግን ይስታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ተግሣጽን የሚቀበሉ ሰዎች ወደ ሕይወት መንገድ ያመራሉ፤ ከስሕተታቸው የማይማሩ ሰዎች ግን አደጋ ላይ ይወድቃሉ። |
እርሱም ይህን ሲናገር ንጉሡ አሜስያስ፥ “በውኑ የንጉሡ አማካሪ ልትሆን ሹሜሃለሁን? ቅጣት እንዳያገኝህ ተጠንቀቅ” አለው። ነቢዩም፥ “ይህን አድርገሃልና፥ ምክሬንም አልሰማህምና እግዚአብሔር ሊያጠፋህ እንዳሰበ አወቅሁ” ብሎ ዝም አለ።
ለሥጋህ በደል አፍህን አትስጥ፥ በእግዚአብሔርም ፊት፥ “ባለማወቅ ነው” አትበል፤ እግዚአብሔር ስለ ቃልህ እንዳይቈጣ፥ የእጅህንም ሥራ እንዳያጠፋብህ፤
ለሚናገረው እንቢ እንዳትሉ ተጠንቀቁ፤ እነርሱ በደብረ ሲና የተገለጠላቸውን እንቢ ስለ አሉት ካልዳኑ፥ ከሰማይ ከመጣው ፊታችንን ብንመልስ እኛማ እንዴታ?
ዐይኑንም አንሥቶ መንገደኛውን በከተማው አደባባይ አየ፤ ሽማግሌውም፥ “ወዴት ትሄዳለህ? ከወዴትስ መጣህ?” አለው።