“ይህን ያህል ዘመን የዋሃን ጽድቅን ሲከተሉ አያፍሩም። ሰነፎች፥ እስከ መቼ ድረስ ስሕተትን ትወዳላችሁ? ሰነፎች ስድብን የሚወዱ ናቸው፥ ሰነፎችም ሆነው ዕውቀትን ጠሉ። ለሚዘልፏቸው የተመቹ ሆኑ፤
ምሳሌ 1:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አላዋቂዎችን አለመመለሳቸው ትገድላቸዋለችና፥ ሰነፎችንም ምርመራቸው ትገድላቸዋለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አላዋቂዎችን ስድነታቸው ይገድላቸዋል፤ ሞኞችንም መታለላቸው ያጠፋቸዋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አላዋቂዎችን ከጥበብ መራቅ ይገድላቸዋልና፥ ሞኞችንም ቸልተኛ መሆን ያጠፋቸዋልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዕውቀት የጐደላቸው ሰዎች ከጥበብ በመራቃቸው ምክንያት ይሞታሉ፤ ሞኞችም ከቸልተኛነታቸው የተነሣ ይጠፋሉ። |
“ይህን ያህል ዘመን የዋሃን ጽድቅን ሲከተሉ አያፍሩም። ሰነፎች፥ እስከ መቼ ድረስ ስሕተትን ትወዳላችሁ? ሰነፎች ስድብን የሚወዱ ናቸው፥ ሰነፎችም ሆነው ዕውቀትን ጠሉ። ለሚዘልፏቸው የተመቹ ሆኑ፤
ነገር ግን እርሱ ከኀያላን ወገን በእርሷ ዘንድ የሚጠፉ እንዳሉ፥ የሲኦል ወጥመድም በቤቷ እንደሚገኝ አያውቅም። ነገር ግን ፈጥነህ ሂድ፥ በቦታዋም አትዘግይ፥ የባዕድን ውኃ እንደምትሻገር በዐይንህ ወደ እርሷ መመልከትን አታዘውትር። ከባዕድ ውኃ ራቅ፥ ብዙ ዘመን ትኖር ዘንድ ከባዕድ ምንጭ ውኃ አትጠጣ። የሕይወትህም ዓመታት ይጨመሩልሃል።
እኔ ግን አዋርዳቸው ዘንድ፥ ስለ ኀጢአታቸውም እበቀላቸው ዘንድ እፈቅዳለሁ፤ እኔ በጠራሁ ጊዜ አልመለሱልኝምና፥ በተናገርሁም ጊዜ አልሰሙኝም፤ በፊቴም ክፉ ነገርን አደረጉ፤ ያልወደድሁትንም መረጡ።”
ክፋትሽ ይገሥጽሻል፤ ክዳትሽም ይዘልፍሻል፤ እኔን መተውሽም ክፉና መራራ ነገር መሆኑን ታውቂያለሽ፤ ትረጂማለሽ” ይላል አምላክሽ እግዚአብሔር፤ “መፈራቴም በአንቺ ዘንድ የለም፤ ይህም ደስ አላሰኘኝም” ይላል አምላክሽ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
በወልድ የሚያምን የዘለዓለም ሕይወት አለው፤ በወልድ የማያምን ግን የእግዚአብሔር የቍጣ መቅሠፍት በላዩ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም።
ለሚናገረው እንቢ እንዳትሉ ተጠንቀቁ፤ እነርሱ በደብረ ሲና የተገለጠላቸውን እንቢ ስለ አሉት ካልዳኑ፥ ከሰማይ ከመጣው ፊታችንን ብንመልስ እኛማ እንዴታ?