Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ምሳሌ 14:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ብልህ ሰው ፈርቶ ከክፉ ይሸሻል፤ አላዋቂ ግን ራሱን ተማምኖ ከኃጥኣን ጋር አንድ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ጠቢብ ሰው ጥንቁቅ ነው፤ ከክፉም ይርቃል፤ ሞኝ ግን ችኵልና ደንታ ቢስ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ጠቢብ ሰው ይፈራል ከክፉም ይሸሻል፥ ሰነፍ ግን ራሱን ታምኖ ይኰራል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ብልኆች እግዚአብሔርን ስለሚፈሩ ከክፉ ነገር ለመራቅ ይጠነቀቃሉ፤ ሞኞች ግን ከአደጋ የማይጠነቀቁ ችኲሎች ናቸው።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 14:16
27 Referencias Cruzadas  

ዐዋቂ ሰው ክፉ ሰው በኀይል ሲቀጣ አይቶ ይገሠጻል፥ አላዋቂዎች ግን ሲያልፉ ይጐዳሉ።


በራስህ አስተያየት ጠቢብ አትሁን፤ እግዚአብሔርን ፍራው፥ ከክፋትም ሁሉ ራቅ፤


ከማናቸውም ዐይነት ክፉ ነገር ራቁ።


የሕይወት መንገዶች ከክፉ ያርቃሉ፤ የጽድቅ ጎዳና የዘመን ብዛት ነው። ትምህርትን የሚቀበል በበጎ ይኖራል። ተግሣጽን የሚጠብቅም ብልሃተኛ ይሆናል። መንገዶቹን የሚጠብቅ ሰውነቱን ይጠብቃል፥ ሕይወትንም የሚወድድ አፉን ይጠብቃል።


እግዚአብሔርን የሚፈልግ ዕውቀትን ከጽድቅ ጋር ያገኛል፥


በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ዮሴፍ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ትድኑ ዘንድ ይህን አድ​ርጉ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እፈ​ራ​ለ​ሁና።


ዔሳ​ውም፥ “ለእኔ ብዙ አለኝ፤ ወን​ድሜ ሆይ፥ የአ​ንተ ለአ​ንተ ይሁን” አለ።


እርሱ አንገቱን ደፍቶ ይከተላታል፥ ለመታረድ እንደሚነዳ በሬ፥ ወደ እስራት እንደሚሄድ ውሻ፥ ሆዱ እንደ ተወጋ ዋሊያ፥


“ተነ​ሥ​ተህ በሰ​ማ​ርያ የሚ​ኖ​ረ​ውን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ንጉሥ አክ​ዓ​ብን ትገ​ናኝ ዘንድ ውረድ፤ እነሆ፥ ይወ​ር​ሰው ዘንድ በወ​ረ​ደ​በት በና​ቡቴ የወ​ይን ቦታ ውስጥ አለ።


ኤል​ዛ​ቤ​ልም፥ “አንተ ኤል​ያስ ከሆ​ንህ እኔም ኤል​ዛ​ቤል ከሆ​ንሁ ነገ በዚህ ጊዜ ሰው​ነ​ት​ህን ከእ​ነ​ዚህ እንደ አንዱ ሰው​ነት ባላ​ደ​ር​ጋት፥ አማ​ል​ክት እን​ዲህ ያድ​ር​ጉ​ብኝ፤ እን​ዲ​ህም ይግ​ደ​ሉኝ” ብላ ወደ ኤል​ያስ ላከች።


ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያ​ንም ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩት ይህን ሲና​ገር ሰም​ተው፥ “እኛ ደግሞ ዕዉ​ሮች ነን?” አሉት።


የአፉ ቃል መጀ​መ​ሪያ ስን​ፍና ነው፥ የን​ግ​ግ​ሩም ፍጻሜ ክፉ ነው።


ሰው​ንም፦ ‘እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት ጥበብ ነው፤ ከክፉ መራ​ቅም ማስ​ተ​ዋል ነው’ ” አለው።


ለወ​ዳ​ጆቼና ለወ​ን​ድ​ሞቼ እን​ደ​ማ​ደ​ርግ አደ​ረ​ግሁ፤ እን​ደ​ሚ​ያ​ለ​ቅ​ስና እን​ደ​ሚ​ተ​ክዝ ራሴን ዝቅ ዝቅ አደ​ረ​ግሁ።


ከእኔ አስ​ቀ​ድ​መው የነ​በ​ሩት አለ​ቆች ግን በሕ​ዝቡ ላይ አክ​ብ​ደው ነበር፤ ስለ እን​ጀ​ራ​ውና ስለ ወይኑ አርባ ሰቅል ብር ይወ​ስዱ ነበር፤ ሎሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ደግሞ በሕ​ዝቡ ላይ ይሰ​ለ​ጥኑ ነበር። እኔ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስለ ፈራሁ እን​ዲህ አላ​ደ​ረ​ግ​ሁም።


የዋህ ነገርን ሁሉ ያምናል፤ ዐዋቂ ግን ወደ ንስሓ ይመለሳል።


ቍጡ ሰው ያለምክር ይሠራል፤ ብልህ ግን ብዙ ይታገሣል።


አህ​ያ​ዪ​ቱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መል​አክ አየች፤ ከበ​ለ​ዓ​ምም በታች ተኛች፤ በለ​ዓ​ምም ተቈጣ፤ አህ​ያ​ዪ​ቱ​ንም በበ​ትሩ ደበ​ደ​ባት።


አው​ስ​ጢድ በሚ​ባል ሀገር ስሙ ኢዮብ የተ​ባለ አንድ ሰው ነበረ፤ ያም ሰው ቅን፥ ንጹ​ሕና ጻድቅ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የሚ​ፈራ፥ ከክፉ ሥራም ሁሉ የራቀ ነበር።


አላዋቂዎችን አለመመለሳቸው ትገድላቸዋለችና፥ ሰነፎችንም ምርመራቸው ትገድላቸዋለች።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios