ምሳሌ 1:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብዙ ሀብቱን እንሰብስብ፥ ከምርኮውም ቤታችንን እንሙላ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ውድ የሆኑ ነገሮችን ሁሉ በየዐይነቱ እናገኛለን፤ ቤቶቻችንንም በዝርፊያ እንሞላለን፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መልካምና ውድ ሀብት ሁሉ እናገኛለን፥ ከምርኮውም ቤታችንን እንሞላለን፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ውድ የሆኑ ብዙ ዐይነት ዕቃዎች እናገኛለን፤ ከቅሚያ በተገኘ ሀብት ቤቶቻችንን እንሞላለን፤ |
በፋርስ ሀገሮችና በግብፅ ሀገሮች ዐውጁና፥ “በሰማርያ ተራሮች ላይ ተሰብሰቡ፤ በውስጥዋም የሆነውን ታላቁን ተአምር፥ በመካካልዋም ያለውን ግፍ ተመልከቱ” በሉ።
ከፊተኛው ይልቅ የዚህ የሁለተኛው ቤት ክብር ይበልጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ በዚህም ስፍራ ሰላምን እሰጣለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።