ምሳሌ 1:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእስራኤል የነገሠ የዳዊት ልጅ የሰሎሞን ምሳሌዎች፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእስራኤል ንጉሥ፣ የዳዊት ልጅ የሰሎሞን ምሳሌዎች፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤል ንጉሥ የዳዊት ልጅ የሰሎሞን ምሳሌዎች፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚህ ምሳሌዎች የዳዊት ልጅ የሆነው፥ የእስራኤል ንጉሥ ሰሎሞን የተናገራቸው ናቸው። |
እግዚአብሔርም እንደ ነገረው ለሰሎሞን ጥበብን ሰጠው፤ በኪራምና በሰሎሞንም መካከል ሰላም ነበረ፤ በመካከላቸውም ቃል ኪዳን አደረጉ።
እነሆ፥ ልጅ ይወለድልሃል፤ የዕረፍት ሰውም ይሆናል፤ በዙሪያውም ካሉ ከጠላቶቹ ሁሉ አሳርፈዋለሁ፤ ስሙ ሰሎሞን ይባላልና፥ በዘመኑም ሰላምንና ጸጥታን ለእስራኤል እሰጣለሁ።
እግዚአብሔርም ብዙ ልጆች ሰጥቶኛልና ከልጆቼ ሁሉ በእግዚአብሔር መንግሥት ዙፋን ላይ ተቀምጦ በእስራኤል ላይ ይነግሥ ዘንድ ልጄን ሰሎሞንን መርጦታል።
“ዛሬስ በምሳሌ ነገርኋችሁ፤ ነገር ግን የአብን ነገር ገልጬ እነግራችኋለሁ እንጂ ለእናንተ በምሳሌ የማልናገርበት ጊዜ ይመጣል።