ለባልንጀራችሁም እንጂ ለየራሳችሁ ብቻ አታስቡ።
እያንዳንዳችሁ ሌሎችን የሚጠቅመውንም እንጂ፣ ራሳችሁን የሚጠቅመውን ብቻ አትመልከቱ።
እያንዳንዱም ሰው የራሱን ጥቅም ብቻ ሳይሆን የሌላውንም ሰው ጥቅም ያስብ።
እንዲሁም እያንዳንዱ የራሱን ጥቅም ብቻ ሳይሆን የሌላውንም ሰው ጥቅም ያስብ።
እያንዳንዱ ለራሱ የሚጠቅመውን አይመልከት፥ ለባልንጀራው ደግሞ እንጂ።
ሙሴም ለሮቤል ልጆችና ለጋድ ልጆች አላቸው፥ “ወንድሞቻችሁ ወደ ጦርነት ሲሄዱ እናንተ በዚህ ትቀመጣላችሁን?
በእኔም ከሚያምኑ ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን የሚያሰናክል ሁሉ፥ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ጥልቅ ባሕር መስጠም ይሻለው ነበር።
ደስ ከሚለው ጋር ደስ ይበላችሁ፤ ከሚያለቅሰው ጋርም አልቅሱ።
የሚገባስ እና ብርቱዎች ደካሞችን በድካማቸው እንድንረዳቸው ነው፤ ለራሳችንም አናድላ።
ለባልንጀራችሁ እንጂ ለራሳችሁ አታድሉ።
ታሞ እኔ የማላዝንለት ማን ነው? በድሎስ እኔ የማልደነግጥለት ማን ነው?
አገልግሎታችንም እንዳይነቀፍ፥ በአንዳች ነገር ማሰናከያ እንዳንሰጥ እንጠንቀቅ።
የክርስቶስን ያይደለ፥ ሁሉም የራሱን ጉዳይ ያስባልና።
ነገር ግን መጽሐፍ “ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ፤” እንደሚል የንጉሥን ሕግ ብትፈጽሙ መልካም ታደርጋላችሁ፤