ፊልጵስዩስ 1:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በፍቅር የሚያስተምሩም አሉ፤ ወንጌልን ለማስተማር እንደ ተሾምሁ ያውቃሉና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህ፣ እኔ ለወንጌል ለመሟገት እዚህ እንዳለሁ ስለሚያውቁ፣ በፍቅር ይህን ያደርጋሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚህ የኋለኞቹ ወንጌልን ለመመከት እንደ ተሾምሁ አውቀው በፍቅር ይሰብካሉ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚህ የእግዚአብሔርን ቃል በቅን ልቡና የሚያበሥሩት ከፍቅር የተነሣ ነው፤ እነርሱም እኔ ለወንጌል ለመከላከል እዚህ የተጣልኩ መሆኔን ስለሚያውቁ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነዚህ ወንጌልን መመከቻ ለማድረግ እንደ ተሾምሁ አውቀው በፍቅር ይሰብካሉ፥ |
የእግዚአብሔርን ቃል በሌላ ቀላቅለው እንደሚሸቅጡ እንደ ብዙዎች አይደለንምና፤ በቅንነት ግን ከእግዚአብሔር እንደ ተላከ በእግዚአብሔር ፊት በክርስቶስ እንናገራለን።
የሚሻለውን ሥራ እንድትመረምሩና እንድትፈትኑ፥ ክርስቶስ በሚመጣበት ቀን ያለ ዕንቅፋት ቅዱሳን ትሆኑ ዘንድ፦
ስለ እናንተ ይህን ላስብ ይገባኛል፤ በምታሰርበትና በምከራከርበት፥ ወንጌልንም በማስተምርበት ጊዜ ከእኔ ጋራ በጸጋ ስለ ተባበራችሁ በልቤ ውስጥ ናችሁና።
እናንተ የፊልጵስዩስ ሰዎች፤ በመጀመሪያው ትምህርት ከመቄዶንያ ወደ እናንተ በመጣሁ ጊዜ፥ ከእናንተ ብቻ በቀር ሌላ ቤተ ክርስቲያን በመስጠትም ቢሆን፥ በመቀበል ከእኔ ጋር እንዳልተባበሩ እናንተ ታውቃላችሁ።
ወንድሜና አጋዤ ስትሪካ ሆይ፥ እንድትረዳቸው አንተንም እለምንሃለሁ፤ ወንጌልን በማስተማር ከቀሌምንጦስና ሥራቸው ከተባበረ፥ ስማቸውም በሕይወት መጽሐፍ ከተጻፈላቸው ከወንድሞቻችንም ሁሉ ጋር ከእኔም ጋር ደክመዋልና።