አብድዩ 1:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በችግራቸውም ቀን በሕዝቤ በር ትገባ ዘንድ፥ በጥፋታቸውም ቀን ጉባኤያቸውን ትመለከት ዘንድ፥ በእልቂታቸውም ቀን በሠራዊታቸው ላይ አደጋ ትጥል ዘንድ አይገባህም ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጥፋታቸው ቀን፣ በሕዝቤ በር መግባት የለብህም ነበር፤ በጥፋታቸው ቀን፣ በጭንቀታቸው መደሰት አልነበረብህም፤ በጥፋታቸው ቀን፣ ሀብታቸውን መዝረፍ አይገባህም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጥፋታቸውም ቀን በሕዝቤ በር ልትገባ፥ በጥፋታቸውም ቀን መከራቸውን ልትመለከት፥ በጥፋታቸውም ቀን በሀብታቸው ላይ እጅህን ልትዘረጋ አይገባህም ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በችግራቸው ቀን ወደ ሕዝቤ በር ልትገባ ባልተገባህ ነበር፤ በመከራቸውም ቀን በይሁዳ ሕዝብ ጥፋት ለመደሰት መተባበር አይገባህም ነበር፤ በመጥፊያቸው ቀን የእነርሱን ንብረት መዝረፍ ባልተገባህም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በጥፋታቸውም ቀን በሕዝቤ በር ትገባ ዘንድ፥ በጥፋታቸውም ቀን መከራቸውን ትመለከት ዘንድ፥ በጥፋታቸውም ቀን በሀብታቸው ላይ እጅህን ትዘረጋ ዘንድ አይገባህም ነበር። |
በእርስዋም ያሉ የተቀጠሩ ሠራተኞች በእርስዋ ተቀልበው እንደ ሰቡ ወይፈኖች ናቸው፤ የጥፋታቸው ቀንና የቅጣታቸው ጊዜ መጥቶባቸዋልና ተመለሱ፤ በአንድነትም ሸሹ፤ አልቆሙምም።
“እግዚአብሔርም በዚያ ሳለ፥ አንተ፥ እነዚህ ሁለቱ ሕዝቦች፥ እነዚህም ሁለቱ ሀገሮች ለእኔ ይሆናሉ፤ እኔም እወርሳቸዋለሁ ብለሃልና፤
የዘለዓለም ጠላት ሁነሃልና፥ በመከራቸውም ጊዜ በኀይለኛይቱ የኀጢአታቸው ቀጠሮ ጊዜ የእስራኤልን ልጆች በሰይፍ እጅ ጥለሃቸዋልና፤
ስለዚህ ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ለቀሩት አሕዛብ ርስት ትሆኑ ዘንድ በዙሪያችሁ ያሉ አሕዛብ አዋርደዋችኋልና፤ ውጠዋችሁማልና፥ እናንተም የተናጋሪዎች ከንፈር መተረቻና የአሕዛብ ማላገጫ ሆናችኋልና፤