አብድዩ 1:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 በጥፋታቸውም ቀን በሕዝቤ በር ልትገባ፥ በጥፋታቸውም ቀን መከራቸውን ልትመለከት፥ በጥፋታቸውም ቀን በሀብታቸው ላይ እጅህን ልትዘረጋ አይገባህም ነበር። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም13 በጥፋታቸው ቀን፣ በሕዝቤ በር መግባት የለብህም ነበር፤ በጥፋታቸው ቀን፣ በጭንቀታቸው መደሰት አልነበረብህም፤ በጥፋታቸው ቀን፣ ሀብታቸውን መዝረፍ አይገባህም ነበር። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 በችግራቸው ቀን ወደ ሕዝቤ በር ልትገባ ባልተገባህ ነበር፤ በመከራቸውም ቀን በይሁዳ ሕዝብ ጥፋት ለመደሰት መተባበር አይገባህም ነበር፤ በመጥፊያቸው ቀን የእነርሱን ንብረት መዝረፍ ባልተገባህም ነበር። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 በችግራቸውም ቀን በሕዝቤ በር ትገባ ዘንድ፥ በጥፋታቸውም ቀን ጉባኤያቸውን ትመለከት ዘንድ፥ በእልቂታቸውም ቀን በሠራዊታቸው ላይ አደጋ ትጥል ዘንድ አይገባህም ነበር። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 በጥፋታቸውም ቀን በሕዝቤ በር ትገባ ዘንድ፥ በጥፋታቸውም ቀን መከራቸውን ትመለከት ዘንድ፥ በጥፋታቸውም ቀን በሀብታቸው ላይ እጅህን ትዘረጋ ዘንድ አይገባህም ነበር። Ver Capítulo |