ዘኍል 9:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም ፋሲካን ያደርጉ ዘንድ ለእስራኤል ልጆች ነገራቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ሙሴ ፋሲካን እንዲያከብሩ ለእስራኤላውያን ነገራቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም የፋሲካን በዓል እንዲያከብሩ ለእስራኤል ልጆች ነገራቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ሙሴ የፋሲካን በዓል እንዲያከብሩ ለሕዝቡ ነገራቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም ፋሲካን ያደርጉ ዘንድ የእስራኤልን ልጆች ተናገራቸው። |
በመጀመሪያው ወር በዐሥራ አራተኛው ቀን በመሸ ጊዜ በጊዜው አድርጉት፤ እንደ ሥርዐቱ ሁሉ እንደ ፍርዱም ሁሉ አድርጉት።”
በመጀመሪያውም ወር በዐሥራ አራተኛው ቀን በሲና ምድረ በዳ ፋሲካን አደረጉ፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው እንዲሁ የእስራኤል ልጆች አደረጉ።