ዘኍል 8:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የመቅረዝዋም ሥራዋ እንዲህ ነበረ። ሁለንተናቸው ወርቅ የሆነ አፅቆችዋ ሥረ-ወጥ ነበሩ፤ አበቦችዋም ሁለንተናቸው ሥረ-ወጥ ነበሩ። እግዚአብሔር ሙሴን እንዳሳየው ምሳሌ መቅረዝዋን እንዲሁ አደረገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የመቅረዙ አሠራር እንዲህ ነበር፤ ከመቆሚያው እስከ አበቦቹ ያለው ከተቀጠቀጠ ወርቅ የተሠራ ሲሆን፣ የመቅረዙም አሠራር እግዚአብሔር ለሙሴ ባሳየው መሠረት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መቅረዙም እንዲህ ሆኖ ተሠርቶ ነበር፤ ከተቀጠቀጠ ወርቅ ተሠራ፤ ከእግሩ እስከ አበቦቹ ድረስ ሥራው ተቀጥቅጦ የተሠራ ነበረ፤ ጌታ ሙሴን እንዳሳየው ምሳሌ መቅረዙን እንዲሁ አድርጎ ሠራው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መቅረዙም እግዚአብሔር ለሙሴ ባሳየው ዕቅድ መሠረት እስከ አገዳውና አበባው ድረስ ከተቀጠቀጠ ወርቅ የተሠራ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መቅረዙም እንዲህ ሆኖ ተሠርቶ ነበር፤ ከተቀጠቀጠ ወርቅ ተሠራ፤ እስከ አገዳውና እስከ አበቦቹ ድረስ ከተቀጠቀጠ ሥራ ነበረ፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳሳየው ምሳሌ መቅረዙን እንዲሁ አደረገ። |
እነርሱም ሙሴ ድንኳኒቱን ሲሠራ ሳለ እንደ ተረዳ፥ ለሰማያዊ ነገር ምሳሌና ጥላ የሚሆነውን ያገለግላሉ፤ “በተራራው እንደ ተገለጠልህ ምሳሌ ሁሉን ታደርግ ዘንድ ተጠንቀቅ” ብሎት ነበርና።