ዘኍል 6:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ለእግዚአብሔር ራሱን የተለየ ባደረገበት ወራት ሁሉ ወደ ሬሳ አይቅረብ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ራሱን ለእግዚአብሔር በለየበት ጊዜ ሁሉ ወደ ሬሳ አይቅረብ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ለጌታ ራሱን በለየበት ወራት ሁሉ ወደ ሬሳ አይቅረብ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በናዝራዊነት በአለበት ጊዜ ሁሉ ወደ ሞተ ሰው በድን አይቅረብ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእግዚአብሔር ራሱን የተለየ ባደረገበት ወራት ሁሉ ወደ ሬሳ አይቅረብ። |
የአምላኩም ቅባት ዘይት ቅዱስነት በላዩ ነውና ከመቅደስ አይውጣ፤ የአምላኩንም ቅዱስ ስም አያርክስ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
ስለዚህ ከአሁን ጀምሮ በሥጋ የምናውቀው የለም፤ ክርስቶስንም በሥጋ ብናውቀው አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ የምናውቀው አይደለም።