ዘኍል 6:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካህኑም የተቀቀለውን የአውራውን በግ ወርች፥ ከሌማቱም አንድ ቂጣ እንጎቻ፥ አንድም ስስ ቂጣ ይወስዳል፤ የተሳለውንም የራስ ጠጕር ከተላጨ በኋላ በባለስእለቱ እጆች ላይ ያኖራቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ናዝራዊው ተስሎ የተለየበትን ጠጕር ከተላጨ በኋላ፣ ካህኑ የተቀቀለውን የአውራውን በግ ወርች እንዲሁም ከመሶቡ ላይ እርሾ የሌለበትን አንድ ወፍራምና አንድ ስስ ቂጣ ወስዶ ናዝራዊው ያስይዘው መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካህኑም የተቀቀለውን የአውራውን በግ ወርች፥ ከሌማቱም እርሾ ያልገባበትን አንድ የቂጣ እንጐቻ እርሾም ያልገባበትን አንድ ስስ ቂጣ ይወስዳል፥ የተቀደሰውንም የራስ ጠጉር ከተላጨ በኋላ በናዝራዊው እጆች ላይ ያኖራቸዋል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ናዝራዊው የተቀደሰውን ጠጒሩን ከተላጨ በኋላ ካህኑ የተቀቀለውን አውራ በግ ወርች፥ በመሶብ ውስጥ ካለው አንድ ኅብስትና አንድ ስስ ቂጣ ወስዶ ናዝራዊ በሆነው ሰው እጆች ላይ ያኖረዋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህኑም የተቀቀለውን የአውራውን በግ ወርች፥ ከሌማቱም አንድ ቂጣ እንጐቻ አንድም ስስ ቂጣ ይወስዳል፥ የተለየውንም የራስ ጠጕር ከተላጨ በኋላ በናዝራዊው እጆች ላይ ያኖራቸዋል፤ |
የእርሱ እጆች ለእግዚአብሔር የእሳቱን ቍርባን ያመጣሉ፤ ፍርምባውን በእግዚአብሔር ፊት ቍርባን ያቀርብ ዘንድ በጉበቱ ላይ ያለውን መረብና የፍርምባውን ስብ ያመጣል።
ሙሴም አሮንንና ልጆቹን አላቸው፥ “ሥጋውን በምስክሩ ድንኳን ደጃፍ በተቀደሰው ቦታ ቀቅሉ፤ አሮንና ልጆቹ ይብሉት ብሎ እግዚአብሔር እንዳዘዘኝ በዚያ እርሱንና በቅድስናው መሶብ ያለውን እንጀራ ብሉ።
“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ወንድ ወይም ሴት ለእግዚአብሔር ራሱን የተለየ ያደርግ ዘንድ ልዩ ስእለት ቢሳል፥
ደግሞም ስቡ ሳይጤስ የካህኑ ልጅ መጥቶ የሚሠዋውን ሰው፥ “ጥሬውን እንጂ የተቀቀለውን ሥጋ ከአንተ አይወስድምና እጠብስለት ዘንድ ለካህኑ ሥጋ ስጠኝ” ይለው ነበር።