ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፣ በመተተኞችና በአመንዝሮች፥ በሐሰትም በሚምሉ፥ የምንደኛውን ደመመዝ በሚከለክሉ፥ መበለቲቱንና ድሀ አደጉን በሚያስጨንቁ፥ የመጻተኛውንም ፍርድ በሚያጣምሙ፥ እኔንም በማይፈሩ ላይ ፈጣን ምስክር እሆንባቸዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ዘኍል 5:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የመርገሙን መራራ ውኃ ለሴቲቱ ያጠጣታል፤ የርግማኑም ውኃ ወደ ሆድዋ ይገባል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ርግማን የሚያመጣውንም ውሃ ሴትዮዋ እንድትጠጣ ያድርግ፤ ውሃውም ወደ ሰውነቷ ገብቶ የመረረ ሥቃይ ያስከትልባታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርግማን የሚያመጣውንም መራራ ውኃ ለሴቲቱ ያጠጣታል፤ የእርግማኑም ውኃ በገባባት ጊዜ መራራ የሆነ ሥቃይ ያመጣባታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሴትዮዋ ብርቱ ሕመም የሚያስከትልባትን መራራ ውሃ እንድትጠጣ ከማድረጉ በፊት፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርግማን የሚያመጣውንም መራራ ውኃ ለሴቲቱ ያጠጣታል፤ የእርግማኑም ውኃ በገባባት ጊዜ መራራ ይሆናል። |
ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፣ በመተተኞችና በአመንዝሮች፥ በሐሰትም በሚምሉ፥ የምንደኛውን ደመመዝ በሚከለክሉ፥ መበለቲቱንና ድሀ አደጉን በሚያስጨንቁ፥ የመጻተኛውንም ፍርድ በሚያጣምሙ፥ እኔንም በማይፈሩ ላይ ፈጣን ምስክር እሆንባቸዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ካህኑም የቅንዐቱን መሥዋዕት ከሴቲቱ እጅ ይወስዳል፤ ያንም መሥዋዕት በእግዚአብሔር ፊት ያቀርበዋል፥ ወደ መሠዊያውም ያመጣዋል፤