ድንበሩ ከባሕሩ በደማስቆ ድንበር ላይ ያለው ሐጽርዔናን ይሆናል፥ በሰሜን በኩል የሐማት ድንበር አለ። የሰሜኑ ድንበር ይህ ነው።
ዘኍል 34:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳርቻውም ወደ ዲፍሮና ያልፋል፤ መውጫውም አርሴናይን ይሆናል፤ በመስዕ በኩል ያለው ወሰናችሁም በዚህ ይሁናችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስከ ዚፍሮን በመቀጠል መጨረሻው ሐጻርዔናን ይሆናል፤ በሰሜን በኩል ያለው ወሰናችሁ ይኸው ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድንበሩም ወደ ዚፍሮን ይዘረጋል መጨረሻውም ሐጸርዔናን ይሆናል፤ ይህ የሰሜን ድንበራችሁ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ዚፍሮን ከተሻገረም በኋላ በሐጻርዔናን ይቆማል፤ ይህም የሰሜን ድንበራችሁ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳርቻውም ወደ ዚፍሮን ያልፋል እስከ ሐጸርዔናንም ድረስ ይወጣል፤ ይህ የሰሜን ዳርቻችሁ ይሆናል። |
ድንበሩ ከባሕሩ በደማስቆ ድንበር ላይ ያለው ሐጽርዔናን ይሆናል፥ በሰሜን በኩል የሐማት ድንበር አለ። የሰሜኑ ድንበር ይህ ነው።
“የነገዶችም ስም ይህ ነው። በሔትሎን መንገድ አጠገብ ወደ ሐማት መግቢያ፥ በደማስቆም ድንበር በአለው በሐጸርዔናን በሐማትም አጠገብ በሰሜን በኩል ይጀምራል። ድንበራቸውም ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ይሆናል። ለዳን አንድ የዕጣ ክፍል ይሆናል።