ዘኍል 34:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር በከነዓን ምድር ለእስራኤል ልጆች ርስታቸውን ይከፍሉ ዘንድ ያዘዛቸው እነዚህ ናቸው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህ በከነዓን ምድር ለእስራኤላውያን ርስት እንዲያከፋፍሉ እግዚአብሔር ያዘዛቸው ሰዎች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ በከነዓን ምድር ለእስራኤል ልጆች ርስታቸውን እንዲያከፋፍሉ ያዘዛቸው እነዚህ ናቸው።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ ለእስራኤል ሕዝብ በከነዓን ምድር ርስት እንዲያካፍሉ እግዚአብሔር የመረጣቸው ሰዎች እነዚህ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር በከነዓ ምድር ለእስራኤል ልጆች ርስታቸውን ይከፍሉ ዘንድ ያዘዛቸው እነዚህ ናቸው። |
ካህኑ አልዓዛር፥ የነዌም ልጅ ኢያሱ፥ የእስራኤልም ልጆች ነገዶች የአባቶች አለቆች በእግዚአብሔር ፊት በሴሎ በምስክሩ ድንኳን ደጃፍ አጠገብ በዕጣ የተካፈሉት ርስት ይህ ነው። ምድሪቱንም መካፈል ፈጸሙ።