La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 33:54 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ምድ​ሪ​ቱ​ንም ትወ​ር​ሳ​ላ​ችሁ፤ በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ች​ሁም ትከ​ፋ​ፈ​ሏ​ታ​ላ​ችሁ፤ ለብ​ዙ​ዎች ድር​ሻ​ቸ​ውን አብ​ዙ​ላ​ቸው፤ ለጥ​ቂ​ቶ​ችም ድር​ሻ​ቸ​ውን ጥቂት አድ​ርጉ፤ እያ​ን​ዳ​ንዱ ሁሉ ዕጣ እንደ ወደ​ቀ​ለት በዚያ ርስቱ ይሆ​ናል፤ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ነገ​ዶች ትወ​ር​ሳ​ላ​ችሁ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ምድሪቱንም በየጐሣዎቻችሁ በዕጣ ተከፋፈሉ። ከፍ ያለ ቍጥር ላለው ሰፋ ያለውን፣ ዝቅተኛ ቍጥር ላለው ደግሞ አነስተኛውን ስጡ፤ ምንም ይሁን ምን በዕጣ የወጣላቸው፣ የየራሳቸው ርስት ይሆናል። አከፋፈሉም በየአባቶቻችሁ ነገዶች አንጻር ይሁን።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ምድሪቱንም በየወገኖቻችሁ በዕጣ ትወርሳላችሁ፤ ለብዙዎች እንደ ብዛታቸው ለጥቂቶቹም እንደ ጥቂትነታቸው መጠን ርስትን ትሰጣላችሁ፤ እያንዳንዱ ሁሉ ዕጣው እንደ ወጣለት በዚያ ርስቱ ይሆናል፤ በየአባቶቻችሁ ነገዶች ትወርሳላችሁ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ምድሪቱንም በተለያዩት ነገዶችና ጐሣዎች መካከል በዕጣ ተከፋፈሉ፤ የጐሣው ቊጥር ከፍ ላለው ሰፊ መሬት ይሰጠው፤ የጐሣው ቊጥር አነስተኛ ለሆነው ደግሞ ጠበብ ያለ መሬት ይሰጠው። እያንዳንዱ ሁሉ ዕጣው እንደ ወጣለት በዚያ ርስቱ ይሆናል፤ በየአባቶቻችሁ ነገዶች ምድሪቱን በርስትነት ትረከባላችሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ምድሪቱንም በየወገኖቻችሁ በዕጣ ትወርሳላችሁ፤ ለብዙዎች እንደ ብዛታቸው ለጥቂቶቹም እንደ ጥቂትነታቸው መጠን ርስትን ትሰጣላችሁ፤ እያዳንዱ ሁሉ ዕጣ እንደ ወደቀለት በዚያ ርስቱ ይሆናል፤ በየአባቶቻችሁ ነገዶች ትወርሳላችሁ።

Ver Capítulo



ዘኍል 33:54
8 Referencias Cruzadas  

ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ርስት ለሌ​ዋ​ው​ያን የም​ት​ሰ​ጡ​አ​ቸ​ውን ከተ​ሞች እን​ዲህ ስጡ፤ ከብ​ዙ​ዎቹ ብዙ፥ ከጥ​ቂ​ቶቹ ጥቂት ትወ​ስ​ዳ​ላ​ችሁ፤ እያ​ን​ዳ​ንዱ እንደ ወረ​ሱት እንደ ርስ​ታ​ቸው መጠን ከከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው ለሌ​ዋ​ው​ያን ይሰ​ጣሉ።”


በተ​ራ​ራ​ማ​ውም ሀገር የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሁሉ ከሊ​ባ​ኖስ ጀምሮ እስከ ማሴ​ሬ​ት​ሜ​ም​ፎ​ማ​ይም መያ​ያዣ ድረስ ሲዶ​ና​ው​ያን ሁሉ፤ እነ​ዚ​ህን ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እን​ዳ​ዘ​ዝ​ሁ​ህም ምድ​ራ​ቸ​ውን ለእ​ስ​ራ​ኤል ርስት አድ​ር​ገህ አካ​ፍ​ላ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሙሴ እጅ እን​ዳ​ዘዘ ለዘ​ጠኙ ነገ​ድና ለእ​ኩ​ሌ​ታው በየ​ር​ስ​ታ​ቸው በዕጣ አከ​ፋ​ፈ​ሉ​አ​ቸው።


የብ​ን​ያ​ምም ነገድ ዕጣ በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው በቅ​ድ​ሚያ ወጣ፤ የዕ​ጣ​ቸ​ውም ዳርቻ በይ​ሁዳ ልጆ​ችና በዮ​ሴፍ ልጆች መካ​ከል ወጣ።