ዘኍል 33:50 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ሙሴን በዮርዳኖስ አጠገብ በኢያሪኮ በኩል በሞዓብ ምዕራብ እንዲህ ብሎ ተናገረው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከኢያሪኮ ማዶ በዮርዳኖስ አጠገብ ባለው በሞዓብ ሜዳ፣ እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ሙሴን በዮርዳኖስ አጠገብ በኢያሪኮ ፊት ለፊት በሞዓብ ሜዳ ላይ እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በኢያሪኮ ትይዩ ከዮርዳኖስ ማዶ በሞአብ ሜዳ ላይ ሳሉ ለእስራኤል ሕዝብ ይነግራቸው ዘንድ እግዚአብሔር ለሙሴ የሚከተለውን መመሪያ ሰጠው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ሙሴን በዮርዳኖስ አጠገብ በኢያሪኮ ፊት ለፊት በሞዓብ ሜዳ ላይ እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ |
የእግዚአብሔርም አገልጋይ ሙሴ እንዳዘዘው፥ ኢያሱ የእነዚህን መንግሥታት ከተሞች ሁሉ፥ ንጉሦቻቸውንም ሁሉ ያዘ፤ በሰይፍም መታቸው፤ ፈጽሞም አጠፋቸው።
እግዚአብሔርም አገልጋዩን ሙሴን እንዳዘዘ እንዲሁ ሙሴ ኢያሱን አዝዞት ነበር፤ ኢያሱም እንዲሁ አደረገ፤ እግዚአብሔርም ሙሴን ካዘዘው ሁሉ ምንም አላስቀረም።