ዘኍል 32:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዮርዳኖስ ወዲህ ወደ ምሥራቅ ርስታችን ደርሶናልና እኛ ከዮርዳኖስ ማዶ ወደዚያ ከእነርሱም ጋር ርስት አንወርስም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ድርሻችንን ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተምሥራቅ ስላገኘን፣ ከዮርዳኖስ ማዶ ከእነርሱ ጋራ የምንካፈለው አንዳችም ርስት አይኖርም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዮርዳኖስ ወዲህ ወደ ምሥራቅ ርስታችን ደርሶናልና እኛ ከዮርዳኖስ ማዶ ከእርሱም ወደዚያ ያለውን ከእነርሱ ጋር ርስት አንወርስም።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኛ የራሳችንን ድርሻ እዚህ ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ ስለ ወሰድን ከዮርዳኖስ ማዶ ለእነርሱ ከተመደበው ርስት ምንም አንወስድም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዮርዳኖስ ወዲህ ወደ ምሥራቅ ርስታችን ደርሶናልና እኛ ከዮርዳኖስ ማዶ ወደዚያ ከእነርሱ ጋር ርስት አንወርስም። |
በእስራኤልም ንጉሥ በፋቁሔ ዘመን የአሶር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር መጣ፤ ኢዮንና አቤልቤትመዓካን፥ ያኖዋንም፥ ቃዴስንና አሶርንም፥ ገለዓድንና ገሊላንም፥ የንፍታሌምንም ሀገር ሁሉ ወሰደ፤ ወደ አሶርም አፈለሳቸው።
የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴም እንደ ሰጣቸው ከእርሱ ከምናሴ ጋር የሮቤልና የጋድ ልጆች፥ በምሥራቅ በኩል በዮርዳኖስ ማዶ ሙሴ የሰጣቸውን ርስታቸውን ተቀበሉ።