ዘኍል 31:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘ ከምድያም ጋር ተዋጉ፤ ወንዶችንም ሁሉ ገደሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ከምድያም ጋራ ተዋጉ፤ ወንዱንም በሙሉ ፈጁት፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ሙሴን እንዳዘዘ ከምድያም ጋር ተዋጉ፥ ወንዶችንም ሁሉ ገደሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት በምድያማውያን ላይ አደጋ ጥለው ወንዶቹን በሙሉ ገደሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘ ከምድያም ጋር ተዋጉ፥ ወንዶችንም ሁሉ ገደሉ። |
የምታደርጉትም ይህ ነው፤ ወንዱን ሁሉ፥ ወንድ የሚያውቁትንም ሴቶች ሁሉ ፈጽማችሁ አጥፉ፤ ደናግሉን ግን አትግደሉአቸው፤” ብለው አዘዙአቸው፤ እንዲሁም አደረጉ።
ዳዊትም ሀገሪቱን መታ፤ ወንድም ሆነ፥ ሴትም ሆነ፥ ማንንም በሕይወት አልተወም፤ በጎችንና ላሞችን፥ አህያዎችንና ግመሎችን፥ ልብስንም ማረከ፤ ተመልሶም ወደ አንኩስ መጣ።